መግቢያ

1

የተተረጎመው መጠን

በዚህ ምዕራፍ:

 • ሚትዩር ለምን ልዩ እንደሆነ ይወቁ።
 • ስለዚህ መጸሐፍ ታሪክ ያንብቡ።
 • ይህ መጸሐፍ እንዴት እንደተቀናበረ ይረዱ።
 • ኣንድ ተሞክሮ እናድርግ። በምዕናቦት ኣንድን ኣቃፊ በሁለት የተለያዩ መስኮቶች ይክፈቱ።

  ኣንደኛውን መስኮት በመጠቀም ኣቃፊው ውስጥ ከሚገኙት ፋይሎች ውስጥ ኣንዱን ያጥፉት። ይህ ፋይል ከሌላኛው መስኮትስ ውስጥ ኣልጠፋምእን?

  ይህን ለመመለስ ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች ማድረግ ኣይጠበቅብንም። በቅርብ ኣካባቢ የፋይል ስርዓታን ውስጥ ኣንድን ነገር ስንለውጥ፤ እኛ ምንም ሳናደርግ ለውጡ በሁሉም ቦታ ይታያል።

  ይህን ሁኔታ ደሞ ወድ ድር እናምጣው። ለምሳሌ ሁለት ኣሳሾችን ከፍተን የኣንድ የዌብፕሬስ ጣቢያ ማስተዳደሪያን ከፍተን ኣንደኛውን ኣሳሽ መስኮት ተጠቅመን ኣዲስ እትም እንፍጠር። ዴስክቶፖ ልይ ካዩት በተለየ ምንም ያህል ቢጠብቁ ሌላኛው የኣሳሽ መስኮት ለውጡን ኣያሳይም፤ እንደገና ገጹን ካልከፈትነው በስተቀር ማለት ነው።

  ለዓመታት ያዳበርነው ግንዛቤ ከድር ጣቢያዎች ጋር መረጃ መቀባበል የሚቻለው ኣጭር እና የማይገናኙ ቁርጥራጭ መልዕክቶች በማሳለፍ ነው የሚል ነበር።

  ይሁንና በኣሁን ጊዜ እየጎረፉ ያሉት ኣዳዲሶቹ ንድፈሃሳቦች እን ቴክኖሎጂዎች ድርን እውን-ጊዜኣዊ እና ቅጽበታዊ በማድረግ ይንን ኣስተሳሰብ ይቀናቀኑታ፤ ምትዩርም ከነዚህ ውስጥ ይገኛል።

  ሚትዩር ምንድን ነው?

  ሚትዩር በኖድ.ጄኤስ(Node.js) ላይ ተመስርቶ የእውን-ጊዜ የድር መትግበሪዎች ማገንባት የሚያስችል የመስሪያ ስርዓት(platform) ነው። በመተግበሪያዎ የውሂብ ቋት እና የተጠቃሚ ኣዋዋይ መሃል በመገኘት የሰመረ ሥራ እንዲሰሩ ያደርጋል።

  በኖድ.ጄኤስ ላይ በመመስቱ ሚትዩር በሁለቱም፤ በተገልጋይ እና በኣገልጋይ ላይ ጃቫስክሪፕትን ይጠቀማል። በተጨማሪም በሁለቱም ወገን ኮድን መጋራት ያስችላል።

  በድር መተግበሪያ ልማት ሂደት ውስጥ የሚገኙትን ብዙዎቹን እክሎች በማስወገድ በጣም ሃይለኛ እና ቀላል የሆነ የመስሪያ ስርዓት ለመፍጠር ተችሏል።

  ሚትዩርን ለምን ይመርጡታል?

  ስለዚህ ሌሎች የድር የመስሪያ ስርዓቶችን ከመማር ይልቅ ሚትዩር ላይ ጊዜዎትን ለምን ያጠፋሉ? የሚትዩርን የተለያዩ ጠቀሜታዎች ትተን ለዚህ መልስ ኣንድ ዋና ሃሳብ ነው፤ ያውም ሚትዩርን መማር ቀላል መሆኑ ነው።

  ሚትዩር ከሌሎች የመስሪያ ስርዓቶች በበለጠ በጥቂት ሰዓቶች ውስጥ ኣንድ እውን-ጊዜኣዊ የድር መተግበሪያ መስራት ያስችለናል። ከዚህ ቀደም ደግሞ የፊት-በኩል(front-end) ልማት ከሰሩ ጃቫስክሪፕትን ያውቁታል፤ ኣዲስም ቋንቋ መማር ኣይኖርቦትም።

  ሚትዩር ልክ የሚፈልጉትን የመስሪያ ስርዓት ሊሆንሎት ይችላል፤ ላይሆንም ይችላል። ነገር ግን ይህን ትምህርት በቀላሉ ሊጀምሩት ስለሚችሉ ለምን ኣይሞክሩትም?

  ይህን መጸሐፍ ለምን ያነቡታል?

  ላለፉት 6 ወሮች ቴሌስኮፕን ላይ ስንሠራ ቆይተናል። ቴሌስኮፕ ሰዎች ማገናኛዎችን እያስገብ እና ድምጽ እየሰጡባቸው የራሳቸውን ማህበረሰባዊ የዜና ጣቢያ (እንድ ሬዲት ወይም ሃክር ኒውስ)) የሚፈጥሩበት የሚትዩር መተግበሪያ ነው።

  ይህን መተግበሪያ ስንገነባ ብዙ ነገሮችን ተመረናል ይሁንና ለነበሩን ጥያቄዎች ሁሌ መልስን ማግኘት ቀላል ኣልነበረም። ከተለያዩ ምንጮች ያገኘናቸውን መረጃዎች እያገጣጥመን፤ ብዙን ግዜ እንዲያውም የራሳችንን መፍትሄ በፈጥረር ለመመለስ ሞክረናል። ስለዚህም በዚህ መጸሐፍ ውስጥ እኝህን የተማርናቸውን ነገሮች ለማካፈል ወደናል እናም ኣንድ የተሟላ የሚትዩር መተገበሪያ ከመጀመሪያው ጀምሮ ቀስ በቅስ መገንባት የሚያስችላችሁን መመሪያ ፈጥረናል።

  የምንሰራው የቴሌስኮፕ ቀለል ያለ ቅጂ፣ ማይክሮስኮፕ የሚባል መተግበሪያ ነው። ይህን ስንገነባ ከኣንድ የሚትዩር መተግበሪያ መሥራት ጋር የሚያያዙ የተለያዩ ክፍሎችን ለምሳሌ የተጠቃሚዎች መለያ፣ የሚትዩር ስብስቦች፣ መንገድ ፍለጋ እና ሌሎችንም እንመለከታለን።

  ይህን መጽሀፍ ካነበብ በኋላ በቀላሉ የቴሌስኮፕን ኮድ መረዳት ይችላሉ።

  ስለደራሲዎቹ

  ስለማነታችን እና ለምን በእኛ ላይ መተማመን እንደምትችሉ ለማወቅ ከፈለጋችሁ፣ ስለኛ ተጨማሪ መረጃ እንኆ።

  ቶም ኮልመንፕርኮሌት ስቱዲዮ ግማሽ ኣካል ነው። ፕርኮሌት ጥራት እና ተጠቃሚነት ላይ የሚያተኩር የድር ልማት ሱቅ ነው። በተጨማሪም የሚትዩራይት እና የኣትሞስፌር የጥቅል ማከማቻ ኣብሮ-ፈጣሪ ሲሆን ከሌሎች ብዙ የምትዩር ክፍት-ምንጭ ፕሮጅክቶችም (እንደ ራውተር) ጀርባ ነው።

  ሳሻ ግሪፍ እንደ ሂፕማንክ እን ሩቢሞሽን ዓይነት ጅማሮዎች ጋር በሥራ-ውጤት እና በድር ዲዛይነርነት ሰርቷል። ቴሌስኮፕን እና ሳይድባርን ፈጥሯል እናም በተጨማሪም የፎልዮ መስራች ነው።

  ምእራፍች እና የጎን ኣሞሌዎች

  ይህ መጸሐፍ ለጀምሪ የሚትዩር ተጠቃሚ እንዲሁም ለላቅ ያሉ ፈርጋሚዎች እንዲጠቅም ስለፈለግን ምዕራፎቹን ለሁለት ከፍለናቸዋል፤ መደበኛ ምዕራፎች (ቁጥር 1 እስከ 14) እና የጎን ኣሞሌዎች (.5 ቁጥሮች)።

  መደበኛ ምዕራፎቹ ያለ ብዙ ሀተታ እንዴት መተግበሪያ መገንባት እና በፍጥነት ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚችሉ እያስተመሮዎታል።

  በሌላ በኩል ደግሞ የጎን ኣሞሌዎች ስለሚትዩር ውስጣዊ ኣሰራር በዝርዝር ይገብበታል። እናም በስተጅርባ ለሚሰራው ሥራ የበለጠ ግንዛቤ ይሰጥዎታል።

  ስለዚህ ጀማሪ ከሆኑ መጸሐፉን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያነብት የጎን ኣሞሌዎቹን ዘለው ማለፍ እንደሚችሉ እና ደግመው ተመልሰው ማንበን እንደሚችሉ ኣይዘንጉ።

  ግብዓቶች እና በጥቅም ላይ የዋሉ ሥራዎች

  ኣንድ የፍርገማ መጸሐፍን ሲያነብ እርሶ እየተከታተሉ የጻፍት ኮድ እና ምሳሌዎቹ ሳይጣጣሙ ሲቀሩ፤ ምንም ነገር ሳይሰራ ሲቀር በጣም ያስከፋል።

  ይህን ለማስቀረት ለማይክሮስኮፕ የጊትሀብ ክምችት ኣዘጋጅተናል። ለእያንዳንዱ የኮድ ለውጥም ወደ ጊት ግብዓት የሚወስዱ ማገናኛዎችንም ኣቅርበናል። በተጨማሪም ከእርሶ ቅጂ ጋር ለማመሳከር እንዲመች እያንዳንዱ ግብዓት ከኣንድ ጥቅም ላይ የዋለ ሥራ ጋር ተገናኝቷል። ለምሳሌ ያህል ከዚህ በታች ይመልከቱ፤

  ኣከማች 11-2

  Display notifications in the header.

  ልብ ይበሉ የይህን ስናደርግ እርሶ ‘git checkout’ በመጠቀም ብቻ መጽሐፍን እንዲዘልቁት ኣይደለም። ይሁንና ጊዜ ሰጥተው በራስዎ ኮዱን በመጻፍ በተሻለ መልኩ ሃሳብን መረዳት ይችላሉ።

  ሌሎች የመረጃ ምንጮች

  የበለጠ ስለሚትዩር መወቅ ቢፈልጉ ዋናው የሚትዩር ስነዳ ጥሩ የመጀመሪያ ቦታ ነው።

  እርዳት ካስፈለግዎ ስታክኦቨርፍሎ(Stack Overflow) ችግርን ለመፍታት እና ጥያቄዎች ለመጠየቅ፤ እንዲሁም #meteor ኣይኣርሲ ቻናል(IRC channel) ለቀጥተኛ እርዳታ እንዲጠቀሙ እንመክራለን።

  ጊት ያስፈልገኛልን?

  ጊት የቅጊ መቆጣጠሪያን መጠቀም መቻል ይህን መጽሐፍ ለማንበብ ኣስፈላጊ ባይሆንም እኛ ግን ማወቁን በኣጽንዖት እንመክራለን።

  ይህን ለማድረግ የኒክ ፍሪናን Git is Simpler Than You Think ገጽ እንዲያነብ እናበረታታለን።

  የጊት ጀማሪ ተጠቃሚ ከሆኑ ማዘዢያ መስምሩን ሳይጠቀሙ ክምችቶችን መቅዳት እና መቆጣጠር የሚያስችሎትን GitHub for Mac መተግበሪያን እንዲጠቀሙ እንመክራለን።

  ያግኙን

  • ሊያገኙን ከፈለጉ በhello@discovermeteor.com ኢሜል ይላኩልን።
  • በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የፊደል ግድፈት ወይም ማንኛውም ዓይነት ስህተት ቢያገኙ በመጽሐፉ የጊትሃብ ክምችት ላይ ጥንቅረ ሳንካ ያስገብ።
  • በማይክሮስኮፕ ኮድ ላይ ችግር ቢያገኙ በማይክሮስኮፕ ክምችት ላይ ጥንቅረ ሳንካ ያስገብ።
  • በመጨረሻም ለሌሎች ጥያቄዎች በመተግበሪያው የጎን ውስን ቦታ ኣስተያየቶን ያስቀምጡልን።